” ለሀገር ዉስጥ በረኞች ትኩረት ለሚሰጡ አሰልጣኞች ትልቅ ክብር አለኝ” መክብብ ደገፉ /የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ/

ትዉልድ እድገቱን በዱራሜ ከተማ አድርጎ እግር ኳስን በፕሮጀክት ታቅፎ በመጫወት ጀምሮ ከዱራሜ ፕሮጀክት አንስቶ እስከ ሀገራችን ትልቁ የዉድድር እርከን እስከ ሆነዉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድረስ መጫወት ከቻለዉ እና በርካታ ክለቦች ላይ በግብ ጠባቂነት ካገለገለዉ እንዲሁም በአሁን ግዜ በሲዳማ ቡና ከሚገኘዉ መክብብ ደገፉ ጋር ሀትሪክ ስፖርት ድህረገጽ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚከተለዉን ቃለ መጠየቅ አድርጋለች።

ሀትሪክ :- በመጀመሪያ ራስህን ለሀትሪክ ቤተሰቦች አስተዋውቅልን ?

መክብብ :- መክብብ ደገፉ እባላለሁ ተወልጄ ያደኩት ዱራሜ ነዉ።

ሀትሪክ :- እስኪ እግር ኳስን የጀመርክበትን አጋጣሚ አጫውተን ?

መክብብ :- እግር ኳስን የጀመርኩት የዱራሜ u15 ፕሮጀክት ላይ በመጫወት ነበር።

ሀትሪክ :- ብዙዉን ግዜ አብዛኞች ተጫዋች መሆንን እንጂ ግብ ጠባቂ መሆንን አይመርጡም እና አንተ በረኝነቱን እንዴት መረጥቅ ?

መክብብ :- በረኝነቱን የጀመርኩት በዋናነት ለበረኝነት ፍቅር ስላለኝ ሲሆን በመቀጠል ደግሞ ብዙ ግዜ ብዙሀን ከሚመርጡት ነገር የተለየ ነገር ማድረግ ስለሚያስደስተኝም ጭምር ነዉ ብዙሀኑ ማይመርጡትን በረኝነቱን የመረጥኩት።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Language »