በኢትዮጵያ ከዱባይ የመጣ ተጨማሪ የቫይረሱ ተጠቂ ተገኘ

በኢትዮጵያ ከዱባይ የመጣ ተጨማሪ የቫይረሱ ተጠቂ ተገኘ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከተቋቋመው የሚኒስትሮች ኮሚቴ ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅት በሰጡት መግለጫም በኢትዮጵያ አምስተኛው የቫይረሱ ተጠቂ መገኘቱን አስታውቀዋል።

ግለሰቡ ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ መሆኑም ታውቋል።

በኢትዮጵያ ከቡርኪና ፋሶ የመጣ ጃፓናዊ የመጀመሪያው የቫይረሱ ተጠቂ መሆኑ ይታወሳል።

ከዚያን ጊዜ ወዲህም ተጨማሪ የቫይረሱ ተጠቂዎች ተገኝተዋል።

FBC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Language »