የአውሮፓ ሀገራት በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በአንድ ቀን ከፍተኛ የሞት መጠን አስመዘገቡ

የአውሮፓ ሀገራት በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በአንድ ቀን ከፍተኛውን የሞት መጠን አስመዝግበዋል።

በቫይረሱ ሳቢያ በጣሊያን 368፣ በስፔን 97 እንዲሁም በፈረንሣይ 29 ሰዎች በአንድ ቀን ለህልፈት መዳረጋቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ከዚህ በተጨማሪም በእንግሊዝ 14 አዲስ ሞት ስታስመዘግብ በድምሩ 35 የሚሆኑ ሰወች በቫይረሱ ለህልፈት ተዳርገዋል።

በመላው አውሮፓ የሚገኙ ሃገራትም የዜጎቻቸውን እንቅስቃሴ በመግታት እና በድንበሮቻቸው የሚያደርጉትን ጥበቃ በማጠናከር የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል።

በአብዛኛዎቹ ሃገራት የሚገኙ ትምህርት ቤቶችም መዘጋታቸው ነው የተነገረው።

በአሁኑ ወቅት የዓለም ጤና ድርጅት አውሮፓ የኮሮና ቫይረስ የወረርሽን ማዕከል መሆኗን አውጇል።

ዓለም ላይ 162 ሺህ 687 ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ፥ 6 ሺህ 65 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል።

ደቡብ አፍሪካም ከቫይረሱ መስፋፋት ጋር በተያያዘ በቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ ከተዛመተባቸው የሚመጡ ሰዎች ድንበሯን ዝግ ማድረጓን ገልጻለች።

ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳም በሃገሪቱ የአደጋ ጊዜ አዋጅን አውጀዋል።

በተመሳሳይ ርዋንዳ የአምልኮ ስፍራዎችን እና ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ወስናለች።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Language »