የ ሀገርን ሰላም ለማስከበር የተንቀሳቀሰው የሲዳማ ክልል ልዩ ሃይል ሽኝት እየተደረገለት ነው

የ ሀገርን ሰላም ለማስከበር የተንቀሳቀሰው የሲዳማ ክልል ልዩ ሃይል ሽኝት እየተደረገለት ነው ሀዋሳ ሀምሌ 7/2013 (ኢዜአ ) ለሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት የሲዳማ ክልል ልዩ ሀይል አባላት ዛሬ ማምሻውን በሀዋሳ ከተማ የሽኝት መርሀ ግብር እየተካሄደ ነው።በመርሀ ግብሩ ላይ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ የክልሉ ካቢኔዎች የሀገር ሽማግሌዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።አቶ አለማየሁ በተለይ ለኢዜአ እንዳሉት የክልሉ ልዩ ሃይል ወቅቱ ለሚፈልገው ሀገራዊ ተልዕኮ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም ግዳጁን ይወጣል።የሀገርን አንድነት ለማፍረስና የህዝብን የተረጋጋ ሕይወት ለማወክ የሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ህግዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባም በዚሁ ወቅት አስረድተዋል።”የልዩ ሃይሉ አባላትም ሀገራዊ ጥሪውን በታላቅ ወኔና ደስታ ተቀብለው ለመዝመት ያላቸው መነሳሳት ከፍተኛ ነው” ብለዋል።በአሁኑ ሰዓት በገዛኸኝ ሆቴል አዳራሽ እየተካሔደ ባለው የሽኝት መርሃ ግብር ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ-መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Language »