በሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ የ2015 በጀት ዓመት የ11 ወራት የሥራ አፈጻጸም ተገመገመ።የሥራ አፈፃፀም መድረኩን የመሩት የክልሉ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ኤልያስ እንደገለጹት የቤተሰብ ብልጽግና ለማረጋገጥ እንዲረዳ አደረጃጀቶቻችን ግባቸውን ማሳካት እንዲችሉ በየጊዜው በመግምገም ጥንካሬያቸውን እና ጉድለታቸውን በመለየት በበጀት ዓመቱ በቀሪ ጊዜያት የታዩ ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ በጀት አመት ዕቅዱ ሳይሸራረፍ ተግባራዊ እንዲሆንና ጠንካራ አደረጃጀት እንዲፈጠር በትጋት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል። ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት አመራሮቻችንና አባሎቻችን የጀመሩትን በግንባር ቀደምትነት ተግባራትን መከወን እንደሚገባ በማንሳት መድረኩ በዋነኝነት በ11 ወራት ውስጥ በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም ጥንካሬ እና ጉድለቶችን በመለየትና በማረም በቀጣይ በጀት አመት በተሻለ አፈጻጸም አደረጃጀቶቻችንን ማጠናከር ላይ በልዩ ትኩረት እንዲሰራ አቶ አሸናፊ ኤልያስ መመሪያ አስተላልፈዋል።በመድረኩም ላይ ምርጥ ተሞክሮዎችን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማስፋት በሚረዳ መልኩ በመንቀሳቀስ በቀሪ ጊዚያት የዓመቱን ሥራዎች በፍጥነት እና በጥራት ለመጨረስ ከስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን በመድረኩም ላይ የሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች የብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊዎችና የክልል ማዕከል የመሰረታዊ ድርጅት አመራሮች የ11 ወር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው ግምገማና ውይይት ተካሂዷል። በሲዳማ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤትሰኔ-12 /2015 ዓ. ም