በሀዋሳና ቢሾፍቱን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

በሀዋሳና ቢሾፍቱን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ስራ በመደገፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

በሃዋሳ ከተማ ስታዲየም እየተካሄደ ባለው መርሃ ግብር ላይ በርካታ የከተማዋ እና የአካባቢው ነዋሪዎች እየተሳተፉ ነው።

የድጋፍ ሰልፉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን፣ መላውን የለውጥ አመራር እና ብልጽግና ፓርቲን ለማበረታታት ያለመ ነው ተብሏል።

ሰልፈኞቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እያመጡት ላለው የለውጥ እንቅስቃሴ እና ለብልፅግና ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍ በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።

በተመሳሳይ ዜና የቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪዎች የድጋፍ ሰፍል እያካሄዱ ነው።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተገኙት ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ለብልፅግና ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍ ገልፀዋል።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ “ብልፅግና ለሁሉም፤ ሁሉም ለብልፅግና፣ ስድብ የኦሮሞ ባህል አይደለም፣ ከዶክተር ዐቢይ ጎን መሰለፍ የኢትዮጵያን ብልፅግና ማረጋገጥ ነው፣ በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር፣ አንድነት ለሰላምና ለብልፅግና” የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።

እንዲሁም የጉጂ ዞን ነጌሌ ከተማ እና የአካባቢው ነዋሪዎች በዛሬው እለት ባካሄዱት ሰልፍ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ለብልፅግና ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍ ገልፀዋል።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተካፈሉ ሰዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ የሰሯቸው ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ባላቸው እውቀት እና አቅም ድጋፍ እንደሚያደርጉም ነው የገለጹት።

FBC

Language »