በአሜሪካ በተፈጸመ የመረጃ መረብ ጥቃት የጋዝ ማስተላለፊያ መስመር ለሁለት ቀናት ተዘጋ

በአሜሪካ በተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ ጣቢያ ላይ የደረሰ የመረጃ መረብ ጥቃት የጋዝ ማስተላለፊያ መስመሩን ለሁለት ቀናት አዘግቷል።

የአሜሪካ የሃገር ውስጥ ደህንነት ተቋም እንዳስታወቀው የመረጃ መረብ ጥቃቱ ለተቋሙ ሰራተኛ በተላከ የኢሜል መልዕክት አማካኝነት የተፈጸመ ነው።

ጥቃት አድራሾቹ የላኩት መልዕክት በኩባንያው የበይነ መረብ አውታር ውስጥ እንዲገባ በማድረግ የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ መስመሩን ለሁለት ቀናት ከስራ ውጭ አድርገውታልም ነው ያለው።

ሆኖም ጥቃቱ መቼና የትኛው ማስተላለፊያ መስመር ላይ እንደተፈጸመ ግልጽ የተደረገ ነገር የለም ነው የተባለው።

ድርጅቱ ለእንደዚህ ዓይነቱ ጥቃት ቀድሞ ስላልተዘጋጀ ሙሉ በሙሉም ባይሆን በከፊል ከባድ ጉዳት እንደደረሰበት ተገልጿል።

ጥቃት ፈጻሚዎቹ ጥቃቱን ለመፈጸም እውነት የሚመስሉ ግን የተጭበረበረ ይዘት ያላቸውን መልዕክቶች እንደሚጠቀሙ ተመላክቷል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሰል ጥቃቶች የተለያዩ የአሜሪካ ድርጅቶችን ኢላማ ማድረጋቸው ይነገራል።

ምንጭ፡- ቢ.ቢ.ሲ

Language »