አማዞን በኮሮናቫይረስ ለተያዙ ሰራተኞቹ ያልተገደበ የህመም ፈቃድ ሰጠ

አማዞን የኮረና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት  በቫይረሱ ለተያዙ ሰራተኞቹ ያልተገደበ የህመብ ፈቃድ  መውሰድ እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡

ተቋሙ ፈቃድ የሚያገኙት ሰራተኞች የኮረና ቫይረስ ምርመራ አድርገው ውጤታቸው ፖዘቲቭ  መሆኑን የሚያሳይ መረጃ ማቅረብ እንዳለባቸው ተመላክቷል።

ከዚህ በፊት በአሜሪካ  የተቋሙ መጋዘን ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ለበዓላት፣ለህመም እና ለድንገተኛ ጉዳዮች  በዓመት አስር ቀናት ብቻ ፈቃድ ይሰጣቸው እንደነበር ተገልጿል፡፡

አንዳንድ ሰራተኞች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለማስቆም አማዞን ፖሊሲውን እንዲለውጥ መጠየቃቸውም ነው የተገለጸው፡፡

በሌላም በኩል በደንበኞች ፍላጎት መጨመርና በሰራተኞች እጥረት አንዳንድ ሠራተኞች ደግሞ  ከመደበኛ የስራ ሰዓታቸው ተጨማሪ ስራ እንዲሰሩ መነገሩን ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

Language »