አየር መንገዱ ዛሬ ወደ መቐለና ላሊበላ የሚያደርገውን በረራ ሰረዘ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛሬው ዕለት ወደ መቐለና ላሊበላ የሚያደርገውን በረራ በአስቸጋሪ የአየር ፀባይ ምክንያት መሰረዙን አስታወቀ።

አየር መንገዱ ዛሬ ጠዋት ወደ ጎንደር፣ አክሱምና ሽሬ ይደረጉ የነበሩ በረራዎች መስተጓጎላቸውንም ጠቁሟል።

በአንዳንድ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች ባጋጠመ አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት የተስተጓጎሉ በረራዎች የአየር ሁኔታው ሲሻሻል የሚቀጥሉ መሆኑ ተመላክቷል።

ከብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ የአየር ፀባይ ምቹነት መረጃ ሲደርሰው በረራውን እንደሚያስቀጥል የገለጸው አየር መንገዱ ፥ይህ የአየር ሁኔታ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ሊቀጥል እንደሚችል ከኤጀንሲው መረጃ ማግኘቱን ጠቁሟል ።

በረራው ሲቀጥል አየር መንገዱ በጥሪ ማዕከሉ በኩል ለደንበኞቹ ጥሪ እንደሚያስተላልፍ ገልጾ፤ ለተፈጠረው መጉላላትም ይቅርታ መጠየቁን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢዜአ

Language »