የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል


አዲስ አበባ፣ ጥር 03፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ተካሂደዋል።

በዚህም ወልቂጤ ከተማን ከሜዳው ውጭ የገጠመው የአምናው ሻምፕዮን መቀሌ 70 እንደርታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ተረክቧል

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ቡናን በሜዳው ያስተናገደው ፋሲል ከነማ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል ።

የፋሲል ከነማን የማሸነፊያ ሁለት ግቦች ሙጂብ ቃሲም ሲያስቆጥር፤ የኢትዮጵያ ቡናን ብቸኛ ግብ ሀብታሙ ታደሰ አስቆጥሯል።

ይህን ተከትሎም ፋሲል ከነማ ፋሲል በፕሪምየር ሊጉ 2ኛ ደረጃን ለመያዝ ችሏል።

በሜዳው ባሕር ዳር ከነማን ያስተገደው ሲዳማ ቡና ደግሞ 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

እንዲሁም የሊጉ መሪ የነበረው ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በሀድያ ሆሳዕና በመሸነፉ መሪነቱን ተነጥቋል።

በተመሳሳይ ስሑል ሽረ ወላይታ ዲቻን 2ለ1 እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሬዳዋ ከተማን 3ለ2 ሲየሸንፉ አዳማ ከተማ ከሐዋሳ ከተማ 1ለ1 ተለያይተዋል።

Language »