ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ የኤርትራ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ


ኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የኤርትራ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከትናንት ጀምሮ በኤርትራ ጉብኝት ሲያደርጉ ቆይተዋል።

በቆይታቸውም የሶስትዮሽ ውይይትን ከኤርትራና ሶማሊያ መሪዎች ጋር አድርገዋል።

ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ ጋር በአስመራ ባደረጉት ውይይት  ከዚህ ቀደም ሀገራቱ የፈረሙትን የሦስትዮሽ ስምምነት ለማስፈጸም ከስምምነት ተደርሷል።

መሪዎቹ መስከረም ወር 2011 ዓ.ም የፈረሙትን የሦስትዮሽ ስምምነት ለማስፈጸም ያላቸውን ቁርጠኝነት ዳግም ማረጋገጣቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

የስምምነቱን አፈጻጸም ከመገምገም ባለፈም ለ2012 እና ቀጣይ ዓመታት የጋራ የሽብር ስጋቶችን ለመቀልበስ፣ የሕገ-ወጥ የሰዎች፣ የመሣሪያ እንዲሁም የአደንዛዥ ዕጽ ዝውውርን ለመግታት የሚሆን የትግበራ ዕቅድ አውጥተዋል።

በተጨማሪም፣ ሦስቱ መሪዎች ሀገራቱ ያሏቸውን የሰው እና የተፈጥሮ ሀብቶች በጥቅም ላይ በማዋል፣ የጋራ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ሥራዎችን ለማከናወን ተስማምተዋል።

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ የሶስትዮሽ ትስስራቸውን የሚያጎለብት የትብብር ስምምነት በመስከረም ወር 2011 ዓ.ም በኤርትራ መፈራረማቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የኤርትራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ሲመለሱም የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአስመራ አውሮፕላን ማረፊያ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።

FBC

Language »