በመላ ሃገሪቱ ትምህርት ቤቶች፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና ትላልቅ ስብሰባዎች ለ15 ቀናት ይዘጋሉ – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ከዛሬ ጀምሮ ትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና ትላልቅ ስብሰባዎች በመላ ሃገሪቱ ለ15 ቀናት እንደሚዘጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በፅህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ በዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ባሉበት ሆነው አስፈላጊው ክትትል ይደረግላቸዋል ብለዋል።

አስፈላጊ ከሆነም አነስተኛ ስብሰባዎች በጤና ሚኒስቴር እውቅና እና ክትትል ሊደገፉ እንደሚገባም ገልጸዋል።

ግብአትን በተመለከተ ሳሙና አልኮልን ጨምሮ ሌሎች የንፅህና መጠበቂያዎች በስፋት እንደሚሰራጩም አስታውቀዋል።

እነዚህን የንፅህና መጠበቂያዎች ሰዎች በቀላሉ እንዲያገኟቸው በተለያዩ አካባቢዎች እንዲቀመጡ ይደረጋልም ነው ያሉት።

Language »