ምክር ቤቱ የሚኒስትሮችን ሹመቶች አፀደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ ሚኒስትሮችን ሹመት አፀደቀ።

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

በመደበኛ ስብሰባውም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀረበለትን የተለያዩ የሚኒስትሮች ሹመት ተቀብሎ አጽድቋል።

በዚህ መሰረት፦

1 ወይዘሮ አዳነች አቤቤ – የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ

2 ዶክተር ሊያ ታደሰ – የጤና ሚኒስትር

3 አቶ ላቀ አያሌው – የገቢዎች ሚኒስትር

4 ወይዘሮ ፊልሰን አብዶላሂ – የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር

ምክር ቤቱም የቀረበለትን የሚኒስትሮች ሹመት በ21 ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።

በዛሬው እለት የተሾሙት ሚኒስትሮችም በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የቀረበለትን የፌደራል

የሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሹመትም አጽድቋል።

በዚህ መሰረት፦

1 አቶ ፀጋ አራጌ – የፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ተሾመዋል።

ምክር ቤቱ የፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሹመቱን በ11 ተቃውሞ፣ በ6 ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።

እንዲሁም ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበለትን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አመራር አባላት ሹመትንም አጽድቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Language »