የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት በኮሮናቫይረስ ተያዙ

የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ባለቤት ሶፊ ግሪጎሪ ትሩዶ በተደረገላቸው ምርመራ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት አስታውቋል።

“የሚመከሩ ጥንቃቄዎችን ሁሉ እየወሰደች ለጊዜው ተገልላ የምትቆይ ይሆናል፤ ደህና ነች የሚታዩባት ምልክቶችም ቀላል የሚባሉ ናቸው።” ይላል የጽሑፉ መግለጫ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ትሩዶ ጤናማና ምንም የኮሮናቫይረስ ምልክቶች የማይታዩባቸው ቢሆንም ለ14 ቀናት ራሳቸውን አግልለው እንደሚቆዩም ተገልጿል።

ነገር ግን ምንም የሚታይባቸው ምልክት ስለሌለ የኮሮናቫይረስ ምርመራ አያደርጉም ተብሏል።

Language »