አንጋፋው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኮቢ ብሪያንትና የ13 ዓመት ልጁ በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው አለፈ


አሜሪካዊው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኮቢ ብሪያንት ከልጁ ጂያና ጋር በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወቱ አለፈ።

ካሊፎርኒያ ካላባሳስ ከተማ በተከሰተው የሄሊኮፕተር አደጋ ኮቢ ብሪያንት እና ልጁን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል።

የ41 ዓመቱ ኮቢ ብሪያንት በግል ሄሊኮፕተር እየተጓዘ በነበረበት ወቅት ሄሊኮፕተሩ ተከስክሶ መቃጠሉን ፖሊስ አስታውቋል።

በደረሰው አደጋ በህይዎት የተረፈ ሰው እንደሌለም ተጠቁሟል።

የአምስት ጊዜ የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ማህበር ሻምፒዮኑ ብሪያንት ለሎስአንጀለስ ሌከርስ ሲጫወት የነበረ ሲሆን በቅርጫት ኳስ ገናና ስም ካላቸው ተጫዋቾች መካከል ይመደባል።

የሃገራት መሪዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ስፖርተኞችን ጨምሮ አድናቂዎቹ በብሪያንት ድንገተኛ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን እየገለፁ ይገኛል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ከአፍሪካ መሪዎች የላይቤሪያው ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊሃ ሀዘናቸውን ገልጸዋል።

በመላው አሜሪካ በተደረጉ የቅርጫት ኳስ ጨዋታዎች ላይ ብሪያንትን በማሳብ የህሊና ፀሎት ተደርጓል።

FANA SPORT

Language »