ኦሞሳዓ ኒውስ ነትዎርክ የኦሞሳዓ ኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ግሩፕ እህት ኩባኒያ ስሆን ከዚህ ሰዓት ጀምሮ መሠረቱን አዲስ አበባ በማድረግ በመላው አለም ያሉ የኦሞሳዓ ልጆችን በማሰባሰብ በኦሞሳዓ ልማት አንድነት እና ለውጥ እንዲመጣ ተግቶ ይሰራል፡፡
በኢትዮጵያ እድገትና ፖሊቲካ ውስጥ ጉሊህ አስተዋጽኦ ማድረግ ካስፈለገ የኦሞሳዓ ልጆች አንድ መሆን አለባቸው ብሎ ኦሞሳዓ ኒውስ ነትወርክ ያምናል፡፡ ለዚህም በህዝቡ አንድነት ላይ በጋራ ባህሉ እና ቋንቋው ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል፡፡ እውነት ለመናገር በጋሞ በወላይታ በዳውሮ በጎፋ እና በኮንታ ህዝቦች መካከል ያለው ልዩነት በኢትዮጵያም ሆኔ ከኢትዮጵያ ውጪ ባሉ ለሎች ህዝቦች መካከል ካለው ልዩነት የተለየ ነው ብለን አናምንም፡፡ ስለሆነም በቋንቋቹ መካከል ያለውን ጥቅት ልዩነት ወደ ጎን በማለት በሚያስተሳስሩን የጋራ ቋንቋና ባህሎች ላይ ትኩረት አድርገን እንሰራለን፡፡
በኦሞሳዓ አዲስ አስተሳሰብና አዲስ እይታ በመፍጠር ወጣቱን በእውቀትና በትምህርት እናበለጽጋለን፡፡ ወጣቱ ጠንክሮ በመማር አፍራሽ እና አሉታዊ የሆኑ አሰራሮችን እና አስተሳሰቦችን እንድዋጋ እናደርጋለን፡፡
ለወጣቱ የአስተሳብ አድማሳሱን የሚያሰፋበት አዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን እናቀርባልን፡፡ ሰው ማለት ከጎሳው በላይ እና የጎሳ ምንጭ ሰው መሆኖን እናስተምራለን፡፡
ባጠቃላይ ከኦሞሳዓ ምድር ክልላዊ ሀገራዊ እና አለም አቀፍ ችግሮችን የሚፈቱ መሪዎችንና የእውቀት ፈጣሪዎችን ለማፍራት ተግተን እንሰራለን፡፡
የኦሞሳዓ ክልልን ተፈጥሯዊ ባህላዊ እና ሰው ሰራሽ መስህበቸን ለአለም በማስተዋወቅ እና ቱሪዝምን በመሳብ እኮኖሚያዊ እድገት ለማምጣት ተግተን እንሰራለን፡፡ ውብና ማራኪ የሆኖ የጋራ ከተሞች እንድገነቡ የራሳችንን አስተዋጽኦ እናደርጋለን፡፡
ባጠቃላይ ለኦሞሳዓ ህዝቦች ሁለንተናዊ እድገት አስተዋጽኦ ለማድረግ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን፡፡
ስለ ሥራ ፈጠራ ስለ ንግድ ስለ አዳድስ የግብርና ተክኖሎጂዎች የኦሞሳዓ ወጣቶችን በከተማና በገጠር እናስተምራለን፡፡ እውቀትን መሠረት በማድረግ የሚሰሩና ብዙ ካፒታል የማይጤይቁ ነገር ግን ብዙ ችግሮችን የሚፈቱ ሥራዎችን እናስተዋዊቃለን፡፡
ኦሞሳዓ ኑ ቢታ ኦማቲያቶ ኑ ዶና!!
ኦሞሳዓ ነውስ ነትወርክ
ለሁለንተናዊ ለውጥ እንተጋለን!!
ጥቅምት 08/2019 አዲስ አበባ