33ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ይጀመራል

33ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ይጀመራል።

የዘንድሮው የጉባኤው መሪ ቃል “ግጭትና ጦርነትን በማስቆም ለአፍሪካ ልማት ምቹ ሁኔታን ማመቻቸት” የሚል ነው።

ለጉባኤው የህብረቱ አባል ሀገራት እና መንግስታት መሪዎች ከአርብ ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ ነበሩ።

በአጠቃላይ በጉባዔው ላይ የ31 የአፍሪካ ሀገራት ፕሬዚዳንቶች፣ 4 ጠቅላይ ሚኒስትሮች፣ የሰባት ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን ጨምሮ የሀገራት ምክትል ፕሬዚዳንቶች እና ቀዳማዊት እመቤቶች እንደሚሳተፉ ነው የሚጠበቀው።

በተጨማሪም የተመድ ዋና ፀሃፊን  ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ ድርጅቶች ሀላፊዎች እና የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ወደ አዲስ አበባ መጥተዋል።

FBC

Language »