በኢትዮጵያ ታሪክ ቀበሌን ከቀበሌ እና ከወረዳ ማዕከል እንዲሁም ከዋና መንገዶች ጋር የሚያገናኝ መንገድ ግንባታ የተጀመረው በ2004 ዓ/ም ነው፡፡ ይህ ሥራ በወቅቱ ለገጠሩ የሀገራችን ህዝብ ከፍተኛ ጥቅም ይዞ የመጣ ሥራ ነበር፡፡ በህደቱ በርካታ ወጣት መሐንዲሶች የመንገድና ዲልድይ አማካሪ እና ተቋራጭ የመሆን እድል ያገኙበት ታላቅ ሥራ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ሥራው ከተጀመረ አምስት ዓመት እነኳን ሳይሞላው የበጀት ችግር የገጠመው እና ከ2010 በኋላ በአብዛኛው ክልሎች የቆሜና በጥቂት ክልሎች ደግሞ በመቆምና ባለመቆም መሀከል ሆኖ የቀጠለ ሥራ ነው፡፡
- አላማው ምን ነበር?
ዋነኛ አላማው 80 ከመቶ በገጠር የምኖረውን የሀገሪቱ ህዝብ ለመሠረታዊ አገልግሎች ማለትም ለትምህርት ጤና እና ውሃ ተቋማት አገልግሎች ቅርብ ማድረግና አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ የገጠሩ ማህበረሰብ ያመረተውን ምርት በቀላሉ ወደ ገበያ ማዕከላት እንድያደርስ ማስቻል ነበር፡፡ ሌላው ዋነኛ አላማ በሀገሪቱ በጣም ዝቅተኛ የሆነውን የመንገድ ነትወርክ ማስፋፋት ስሆን በህደቱም ሀገር በቀል የሆኑ አማካሪዎችን እና ተቋራጮችን በብዛት ማፍራት ዋነኛ አላማው ነበር፡፡
- ምን ችግሮች አጋጠሙ?
በዋናነት መጀመሪያ ያጋጠሙ ችግሮች የዕውቀትና የፕሮጀክት አመራር ችግር ስሆኑ አብዛኛዎቹ ሥራውን የተቀላቀሉ መሐንዲሶች ተመሳሳይ ልምድ ያልነበራቸውና እና ለሥራው አዲስ መሆናቸው በዲዛይን ዝግጅትና በግንባታ ትግበራ ወቅት ከፍተኛ ችግር ፈጥሮ ነበር፡፡ በመንግስት በኩል ሥራውን ለመተግበር የተዘጋጀበት መንገድ ከፍተኛ ክፍተት የነበረበትና ሥራውን ወደ መረት ለማውረድ ጥቅም ላይ ለማዋል የታሰበው ቴክኖሎጂ ከጊዜው ጋር የማይሄድ እና እጅግ በጣም ሁዋላ ቀር ነበር፡፡ ይህም በፕሮጀክቱ ትግበራ ላይ የራሱ የሆኔ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሮ አልፏል፡፡ እነዚህና ለሎች ተያያዥ ችግሮች መጀመሪያ ያጋጠሙ ከባድ ፈተናዎች ስሆኑ እነዝህ በመጠኑ ስፈቱ በኋላ ላይ ያገጠመው የበጀት ችግር ዋነው ፈተና ነው፡፡
- ምን ሲኬት ተገኜ?
አሁን ላይ ስንገመግመው በችግሮች ውስጥ ሆኖ ከተገነቡ ጥቂት መንገዶች ውጪ እና እነዚህም መንገዶች በአሁኑ ወቅት ከጥቅም ውጪ በመሆናቸው ከአላማዎቹ አንዱንም አሳክቷል ማለት አይቻልም፡፡
- ምን ትምህርትና ልምድ ተወሰደ?
እንደዚህ አይነት ትላልቅ ክልላዊ እና ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ስታቀዱ አስቀድሞ ዘጎችን እና አመራሩን በዕውቀት ማብቃት እና ወቅቱን የሚመጥን እውቀትና ክህሎት ማስታጠቅ ያስፈልጋል፡፡ ካልሆነ የሀገርንና የህዝብን ሀብት በከንቱ ማባከን ይመጣል፡፡
- አሁን ምን መደረግ አለበት?
አሁን ላይ ከውድቀቱ የተማሩ እና እስከ አሁን የዘለቁ አማካሪዎችን እና ተቋራጮችን የበለጠ በማብቃትና ባለፉት 15 ዓመታት ወደ ገበያው የተቀላቀሉ መሐንዲሶችን ባለው ሚቹ ሁነታ ወደ አማካሪነትና ተቋራጭነት እንዲገቡ በማበረታታትና የተለያዩ አጫጭር ስልጠናዎችን በማመቻቸት በቀጣይ ለሚተገበሩ ታላላቅ ክልላዊና ሀገራዊ ፕሮጅቶች ማዘጋጀት ያስፈልጋል እንላለን፡፡