የጥምቀት በዓል እየተከበረ ነው

ጥምቀት በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በመከበር ላይ ይገኛል።

በመላ ሀገሪቱ ትናንት ታቦታት ከአድባራት ወጥተው በካህናት፣ በዲያቆናት እና በምዕመናን ታጅበው ወደ ጥምቀተ ባህሩ ማደራቸው ይታወቃል።

ከዛሬ ማለዳም ጀምሮ የጥምቀት በዓል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች በመከበር ላይ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ጃን ሜዳ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የእምነቱ አባቶች እና መሪዎች እንዲሁም ምእመናን በተገኙበት በድምቀት የጥምቀት በዓሉ እየተከበረ ይግኛል።

FBC

Language »